• (+251)462125955
 • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

መግቢያ

 1. የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ ያዘጋጃል፤ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በማቅረብ ያስፀድቃል፤
 2. የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና መልክዓ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ያደራጃል፤ ትንተና በማድረግ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፤
 3. የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልክዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስና ካርታ ያዘጋጃል፤
 4. የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች በሥራቸው ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ የማድረግ እንዲሁም ስታንዳርዱንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ድጋፍ፣ ክትትልና ኦዲት ያደርጋል፤ በመረጃዎች ኦዲት ግኝት መሠረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
 5. የክልሉን የመረጃ ክፍተት ለማሟላት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያከናውናል፤
 6. የክልሉን የስታቲስቲክስና መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራውን ያስተባብራል፤ ይመራል፤
 7. የሥነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፤
 8. በሥነ ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ሥራዎችን ያካሂዳል፤
 9. የሥነ ህዝብና ልማት ጉዳዮችን በተመለከተ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ያከናውናል፤
 10. በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ ህዝብ ምክር ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ5 ዓመት የሥነ ህዝብ ፕሮግራም ያዘጋጃል፤ ለሥነ ህዝብ ም/ቤቱ በማቅረብ ያስፀድቃል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል፤
 11. በዕቅድና ፕሮጀክቶች ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤
 12. ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡