• (+251)462125955
  • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

የስራ ክፍሎች

(GIS & Geospatial Development Dtrectorate) ማለት በክልሉ የመልክዓምድርና የካርታ መረጃ በማሰባሰብ ለዕቅድ ለአስተዳደራዊና ልማት ሰራ በየአሰተዳደር እርከን በማደራጀት የካርታ መረጃ ጥያቄዎችን ፍላጎት ለተገልጋዮች ምላሽ መሰጠት ነዉ’ በዚህም መሰረት የጂኦሰፓሻል አሰራርን በመከተል የካርታ መረጃ ማዕከል በመሆን የተገልጋዮችን የመረጃ ፍላጐት እያጠና ደረጃውን የጠበቀ የየአስተዳደር እርከን በጂአይኤስ ሶፍትዌር በመጠቀም የካርታ መረጃ በነጠላ ካርታና በአትላስ ዶክመንት አዘጋጅቶ ማቅረብ ነዉ’ ከፌደራል መ/ቤቶች& ከየአስተዳር አርከንና ከየሴክተር መ/ቤቶች እንዲሁም ከሌሎች ምንጮች የጂኦስፓሻልና ካርታ መረጃ በመሰብሰብ፣ የጂአይኤስ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ዘመናዊ የጂአይኤስ ዳታቤዝ በማደራጀትና በመተንተን በሀርድና ሶፍት ኮፒ በማዘጋጀት በድረ-ገጽ እና በሌሎች በተለያዩ መንገዶች ለተገልጋች ተደራሽ የማድረግ ስራ ይሰራል

Statistical data Quality, control & assurance directorate) ማለት የክልሉ የመረጃ ጥራትና ቁጥጥር ማዕከል በመሆን የተገልጋዮችን የመረጃ ፍላጐት እያጠና ደረጃውን የጠበቀ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ሰታቲስቲክስ ዳታ ፣ በዘመናዊ ዳታቤዝ እና አኘሊኬሽን ሶፍትዌሮችን ጥቅም ላይ እንዲዉል አሰራር ይፈጥራል’ በኢኮኖሚና ማህበራዊ በየሴክተሩና በየአስተዳደር እርከን የሚደራጁ መረጃዎችን ጥራታቸዉንና ሰታንዳርዳቸዉን በመቆጣጠር በጥራት፣ ማደራጀታቸዉንና መተንተኑን በማረጋገጥ መረጃዎች ለተጠቃሚ ተደራሽ መሆናቸዉን ያረጋግጣል::

የሶሽዮ-ኢኮኖሚና ሥነ-ሕዝብ ስታቲስቲክስ ዳይሬክቶሬት (Socio-Economic & Population Statistics Directorate)
ማለት የክልሉ የኢኮኖሚ& ማህበራዊና ሥነሕዝብ ስታቲስቲክስ መረጃ ማዕከል በመሆን የተገልጋዮችን የመረጃ ፍላጐት እያጠና ደረጃውን የጠበቀ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ሥነሕዝብ ሰታቲስቲክስ መረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎችን /tools/ በማዘጋጀት መረጃዎችን ከመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ከሆኑት አስተዳደራዊ እርከኖችና የሴክተር መ/ቤቶች እንዲሁም ከሌሎች ህጋዊ ተቋማት በመሰብሰብ፣ ዘመናዊ ዳታቤዝ እና አኘሊኬሽን ሶፍትዌሮችን ተጠቅሞ በማጠናቀር፣ በማጥራት፣ በማደራጀትና ጥናቶችን በማካሄድ በመተንተን በሀርድና ሶፍት ኮፒ በማዘጋጀት በድረ-ገጽ እና በሌሎች በተለያዩ መንገዶች ለተገልጋች ተደራሽ የማድረግ ስራ ይሰራል’