• (+251)462125955
  • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

ግቦች

1) የረጅም፤የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ስርዓት በመዘርጋት የአፈጻጸም ውጤታማነት ማሳደግ፤
2) የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ግምገማ ስልትን ማሳደግ፤
3) በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ፤
4) ስራ ዕድል ፈጠራናን በማሳደግ የስራ አጥን ቁጥር መቀነስ፤

5) የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥን በወሳኝ መልኩ ማረጋገጥ፤
6) በማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾች ላይ ጥናት በማድረግ ለቀጣይ ዕቅዶች ግብአት እንዲሆኑ ማስቻል
7) ክልላዊ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል አሰራርን በማዘመን ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ፤
8) ክልላዊ የካፒታል ኘሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ፣
9) በክልሉ የሚተገበሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከትግበራ በፊት የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ማካሄድና ፍትሃዊ ስርጭቱን ማረጋገጥ፤
10) ከጽንሰ ሀሳብ እስከ ድህረ ትግበራ በፕሮጀክት አስተዳደር ዙርያ ክፍተቶችን በመለየት ፍለጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ማሳደግ፤
11) የክልሉ ስታቲስቲካዊ መረጃ አቅርቦት በጥራት፤ በግዜ እና በመጠን የተሟላ በማድረግ የተገልጋይ ፍላጎትና እርካታ 100 % ማረጋገጥ፤
12) በክልሉ አስተዳደራዊ ሰታቲስትካል መረጃ አመንጭ ተቋማት የመረጃ አስተዳደር ሂደትና ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ የመረጃ ጥራት ችግር በወሳኝ መልኩ 95 በመቶና በላይ በመፍታት ዉጠታማነትን ማረጋገጥ፤
13) በናሙና ጥናት (sample survey) እና ሙሉ ቆጠራ (census) ዘዴዎችን በመጠቀም የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና የሚለካባቸዉ መለክያዎች የሚፈልጋቸዉን መረጃዎች መቶ በመቶ በማመንጨት የመረጃ አቅርቦት ችግርን በመቅረፍ የአሰራር ቅልጥፍናን መጨመር፤
14) የሰው ሃብት ብቃትና ተነሳሽነትን ማሳደግ
15) የክልሉ ስታቲስቲካል ሲስተም (Regional statistical system) የሚመራባቸዉ የሕግ ማዕቀፎች፤የአሰራር ሥርዓቶችን መዘርጋትና የተዛቡና ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን በሚያቅርቡ አካላት የተጠያቂነት አሰራርን ማስፈን እንዲሁም የተቋማዊ ብቃት ደረጃዎች በማጠናከር ለሀገራዊዉ ስታቲስቲካል ሲስተም ሞዴል እንዲሆን ማስቻል፤

የሁሉም ዓይነት መረጃ መሰብሰብያ ዘዴዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ በማድረግ እና ለዚህም የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ሙሉ በሙሉ እንድሟሉ በማድረግ የመረጃ አሰባሰብ ዘደዉን ማዘመን፤
17) ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብአት በማሟላትና በመጠቀም የገፀ-ምድርና ከርሰ-ምድር መረጃዎችን በማሰባሰብ፤በማደራጀት እንዲሁም በዘመናዊ ጂኦ-ዳታ ቤዝ በማከማቸት፤በመተንተንና በተለያዩ ሰነድ ዓይነቶች (በካርታ፤በአትላስ፤በቡክሌትና ወዘተ) ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የተጠቃምዎችን እርካታ 100 በመቶ ማድረስ፤
18) የክልሉ ማዕከላዊ መረጃ ክፍል (Regional data center) የመረጃ መረብ ደህንነት ተጠብቆ የማከማቸትና የማሰራጨት አቅም ሀገር አቀፍ ደረጃዉን በጠበቀ መንገድ እንድቋቋም በማድረግ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ማሻሻል፤
19) ክልላዊ ስታቲስቲካል ሲስተም ሪፎርም ፕሮግራም፣በማጥናት፣ ዕቅድ በማዘጋጀትና የትግበራ ሥርዓቱን በመከታተል ዉጤታማነቱን ማረጋገጥ፤
20) ክልላዊ ስታትስቲካል መረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት አሰጣጥ በመዘርጋት (authentication of official statistics of the region) መቶ በመቶ የመረጃ ቁጥጥር በማረጋገጥ አገልግሎትን መጨመር፤
21) በሥነ-ህዝብና ልማት ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ 100% ማሳደግ፤
22) የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ አሁን ካለበት 2.9 ወደ 2.3 በመቶ ማድረስ፤
23) ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ልማት ማረጋገጥ፤
24) የሴቶችና ወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማሳደግ
25) ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማካሄድ የሥነ-ህዝብና ልማት ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ መፍታት፤