• (+251)462125955
  • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

ዶ/ር ባዩሽ ተስፋዬ

እንኳን ወደ ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ድረገፅ በሰላም መጣችሁ፡፡
ቢሮዉ የክልሉን የመረጃ ክፍተት ለማሟላት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያከናዉናል፣ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀማቸዉን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አፈፃፀም ጥናት ያካሂዳል፣ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ለመስተዳድር ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፣ የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል፤ ይገመግማል፤ ያስፀድቃል፣ በክልሉ የታችኛዉን የአስተዳደር ዕርከን ዓመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል፣ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፣ የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸዉ አካላት ያቀርባል፣ የልማት ክፍተት እና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል፣ የክልሉን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ጥናት ያደርጋል፣ የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ያስፀድቃል፣ የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በማቅረብ ያስፀድቃል፣ የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና መልክአ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፤ ትንተና በማድረግ አሳትሞ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልክዓ ምድራዊ ገፅታን የሚያሳይ አትላስና ካርታ ያዘጋጃል፣ የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶች በሥራቸዉ ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ እንዲሁም ስታንዳርዱንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ድጋፍ፣ ክትትል እና ኦዲት ያደርጋል፣ በመረጃዎች ኦዲት ግኝት መሠረት ተገቢዉን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ የክልሉን የስታቲስቲክስ መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራዉን ያስተባብራል፤ይመራል፣ የሥነ- ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፣ በሥነ- ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጐልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ሥራችን ያካሂዳል፣ የሥነ- ህዝብና ልማት ጉዳዮችን በተመለከተ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ያከናዉናል፣ በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ- ህዝብ ም/ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ5ዓመት የሥነ-ህዝብ ፕሮግራም ያዘጋጃል፣ ለሥነ- ህዝብ ም/ቤቱ በማቅረብ ያፀድቃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል አቅጣጫ ያስቀምጣል፣ በዕቅድና ፕሮጀክቶች ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፣ የክልሉን የአስር ዓመት ዕቅዶችን በማቀድ ማሳተምና ማሰራጨት፣ በክልሉ ዉስጥ በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃዎችን በማራጀት ለየተቋማት አሰራርን በመዘርጋት፣ የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማድረግ ፣ በአዋጅ በተሰጠዉ ስልጣንና ተግባር መሠረት በበላይነት የመምራት ኃላፊነት አለበት፡፡
ዶ/ር ባዩሽ ተስፋዬ አየለ
በም/ል ር/መ/ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር
አስተባባሪና ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ