- የዳይሬክቶሬቱን ስራዎች በመምራት እና በማስተባበር፣ የኦዲት አሰራሮችን ለማሻሻል የመከናወኑ ጥናቶች፣ የክትትልና ድጋፍ ተግባራትን በመምራትየመንግስት ሃብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ ነው፡፡
- የዳይሬክትሬቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ ለባለሙያዎች ያከፋፍላል
- የዳይሬክትሬቱን ለስራ አስፈላጊ የሁኑ ግብዓቶች እንዲሟሉ ያደርጋል
- የዳይሬክተሩን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን ይዘረጋል፤ ስልቶችንም ይነድፋል፡፡
- የዳይሬክቶሬቱን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሉ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ይዘረጋል፡፡
- በዳይሬክቶሬቱ ሥር ያሉ ፈጻሚ ባለሙያዎች አቅማቸው እንዲገነባ ያደርጋል፤
- የባለሞያውን የስራ አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- መ/ቤቶች የውስጥ ኦዲት የአሰራር ችግሮች በጥናት እንዲለዩ ያደርጋል፡፡
- የውስጥ ኦዲትን የሚመለከቱ በባለሙያዎች የሚቀርቡ የፖሊሲ ሃሳቦችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ ያጠቃልላል፡፡
- የውስጥ ኦዲት አሠራር በተመለከተ በባለሙያዎች የሚቀርቡ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶች፣ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ እንዲጸድቅ ያደርጋል፤፤
- ከውስጥ ኦዲት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በዓለምና አገር አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲካሄዱ አሰፈላጊውን ነገር ያመቻቻል፡፡
- በባለበጀት መ/ቤቶች አሰራሮች ውጤታማ የሆነ የውስጥ ኦዲት አደረጃጀት ለመፍጠር የሚካሄዱ ጥናቶችን በበላይነት ያስተባብራል፤የሚቀርቡ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ ያጸድቃል፡፡
- የውስጥ ኦዲት በሥራው ምክንያት የሚደርስበትን ተጽእኖ እንዲጣሩና መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- የውስጥ ኦዲት አሰራርን በተመለከተ የበላይ ኃላፊዎችና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጫበቻ ስልጠናዎችና የውይይት መድረኮች እንዲዘጋጁ አስፈላጊውን ነገር ያመቻቻል፡፡
- ከሙያና ከስልጠና ተቋማት ስልጠናዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ፕሮጀክት እንዲቀረጹ ያደርጋል፤ ስልጠናዎችንም ያፈላልጋል፣
- የኦዲት እቅድ ዝግጀት እና የስጋት አካባቢዎችን የመለየት የሚደረጉ ጥናቶችን ያስተባብራል፤ በበላይነት ይመራል፡፡
- በተቋማት የአስተዳደር ሥርዓት /Governance/ እንዲገመገም ያደርጋል፡፡
- በተለዩት የስጋት አካባቢዎች መስረት የፋይናሻል፣ የሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት እንዲሁም የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ሂደቱንም በበላይነት ያስተባብራል፤ይመራል፤
- በባለሙያዎች የሚቀርቡ የፋይናሻል፣ የሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት እንዲሁም የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ የኦዲት ሪፖርቶች በመገምገም እንዲጠቃለሉ ያደርጋል፡፡
- በኦዲት መውጫ ስብሰባ ላይ በመገኘት ስብሰባውን ይመራል ያወያያለ፤
- በውይይቱ ወቅት በተደረሰባቸው ስምምነቶች መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበለትን የኦዲት ሪፖርት ትክክለኛነት አረጋገጥ ያስተላልፋል፤
- የውስጥ ኦዲት አሠራር በተመለከተ የተዘጋጁ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን በአግባቡ ተግባራዊ መደረጋቸውን ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤
- ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚቀርቡ የውስጥ ኦዲት እቅዶችንና ሪፖርቶችእንዲገመገሙ በማድረግ የማሻሻያ ሃሳቦችንለተቋማት ይልካል፡፡
- መ/ቤቶች ኦዲቱ ሲከናወን በተዘጋጀው የኦዲት ፕሮግራም መሰረት ሥራው እየተከናወነ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- በውስጥና በውጪ ኦዲተሮች በተሰጡ የኦዲት አስተያየትና ማሻሻያ ሃሳቦች መሰረት የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች በአግባቡ መገምገሙንይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡፡
- በባለሙያዎች የሚቀርቡ የመ/ቤቶች የተጠቃለለ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግና በማጸደቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲላክ ያደርጋል፡፡
- በመ/ቤቶች አንኳር የኦዲት ግኝቶች ሪፖርት ላይ ተመስርቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጠ አመራር ተፈጻሚነትን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ በተመለከተ ለባለሙያዎች የተሰጡ ስልጠናዎች የመጡትን ለውጥ ይከታተላል፤ይገመግማል፣
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
- በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
- በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
- ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡