- የተቋሙን አደረጃጀትና የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ጥናቶችን በየጊዜው በማጥናት ደንብና መመሪያን መሠረት በማድረግ የተቋሙን ዕቅድና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል የሰው ሀብት እንዲሟሉ ያገርጋል፤
- አዲስ የሰው ኃይል ፍላጎት ለሚያቀርቡ የሥራ ክፍሎች እንደ አስፈላጊነቱ ጥናት በማካሄድና የሥራ ደረጃውን በመወሰን ለሚመለከተው ተቋም ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በደንቡ መሠረት ይፈጽማል፣
- በተቋሙ አደረጃጀት መሠረት በየሥራ መደቦች ተገቢው የሥራ ዝርዝር እንዲዘጋጅ በማድረግና በመገምገም የማሻሻያ ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ተፈጻሚነቱንም ይከታተላል፣
- በተቋሙ የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር መመሪያዎችና ማኑዋሎችን ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነቱን በመከታተል እንዲሻሻል ያደርጋል፣
- የተቋሙ ድርጅታዊ መዋቅር በሚሻሻልበት ጊዜ ጥናት በማድረግና ለሚመለከተው ያቀርባል ሲፈቀድ ተገቢውን በማሟላት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
- የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎችን ያደራጃል፣ ያጠናቅራል፣ ከሌሎች ሙያተኞች ጋር በመተባበር የተቋሙን አደረጃጀት ያጠናል፣
- ከተቋሙ በሚደርሰው የሰው ኃይል ፍላጎት መጠየቂያ ቅጽ መነሻ በማድረግ ለቅጥር፣ ለደረጃ ዕድገትና ለዝውውር ደንብና መመሪያ መሠረት በማድረግ ማስታወቂያ ያወጣል፣
- በማስታወቂያ መሠረት የተመዘገቡ አመልካቾችን መረጃ ያጣራል፣ ምርጫ እንዲከናወን በማድረግ ያጸድቃል፣
- ፈተና በማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ በማድረግ ተወዳዳሪዎችን በመፈተን የፈተናውን ውጤት ያሳውቃል፣
- የተቀጠሩ ሠራተኞች የተቋሙንና የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንቦችና መመሪያዎችን እንዲያውቁ ያደርጋል፣
- በተቋሙ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ህግንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
- በተቋሙ ላሉ ሠራተኞች የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ጭማሪ የሚገባችውን ሠራተኞች በመለየትና በጀት እንዲያዝላቸው በማድረግ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣
- የተቋሙን ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና መረጃ በየ6 ወር በትክክል መሞላቱን በማረጋገጥ ያጠናቅራል፣
- ለሠራተኞች በደንብና መመሪያ መሠረት የተፈቀዱ ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን፣ የስራ ልብስ፤ የስራ መሣሪያ፣ የተለያዩ አበሎች እና የደረጃ እድገት የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎች እንዲማሉ በማድረግ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
- በዲሲፕሊን ግድፈት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በህጉ መሠረት በማጣራት የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል።