የሶሺዩ ኢኮኖሚ ፕሮፋይል ጥናትና ጂ አይ ኤስ ዳይሬክቶሬት
የዳይሬክቶሬቱ ኃላፊነትና ዋና ዋና ተግባራት
- በክልሉ የሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ ልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ተግባራትን በጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመደገፍ ዉጤታማነታቸዉን ለማሳደግ ይሰራል፡፡
- የጂኦስፓሻል ሲስተም አርክቴክቸር እና የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሥነ ምህዳር ዲዛይን ሥራን ያስተባብራል፡፡
- የክልሉን የሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና የጂኦስፓሻል መረጃዎችን ያደራጃል፡፡
- በየአስተዳደር እርከኑ የሚካሄዱ የሶሽዩ-ኢኮኖሚ ፕሮፋይሎችን ዝግጅት ያስተባብራል፡፡
- ክልላዊ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መሰረተ-ልማቶችን ሥርጭት(Urban &rural facilities and Infrastructure data) መረጃዎችን ስታንዳርድ ኮዶችን በመጠቀም በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲሰበሰቡ ያደርጋል፡፡
- የመረጃዎችን ጥራት ይቆጣጠራል፤ወቅታዊነት እና ተአማኒነትም ያረጋግጣል፡፡
- የክልሉን የማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና የተፈጥሮ ሀብቶችን የሚያሳዩ ’ÖL ካርታዎችን (thematic map) እና አትላሶች ያዘጋጃል፡፡
- ለተቋማትና የሥራ ዘርፎች የሚያገልግሉ የሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን ከልማት አመላካቾች(Development Indicators) ጋር ተቃኝተዉ እንዲዘጋጁ ያደርጋል፡፡
- በክልሉ አዳዲስ መልካዓምድር ነክ (Geo-spatial data) Satellite Images, Arial photographs መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ዘዴዎችንና ቴክኖሎጂዎችን (GPS,GIS &RS) ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- በጂ.አይ.ኤስ እና ሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ የተገኙ የሳተላይት ምስሎች (Satellite Images) የአየር ፎቶግራፎች እንዲሁም በምድር ላይ ቅየሳና በጂ.ፒ.ኤስ የሚሰበሰቡ የጂኦስፓሻል መረጃዎችን በማጠናቀርና በመተንተን የዉሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
- ሶፍትዌሮችን በማልማትና በማላመድ ዘመናዊ እና ደረጃውን የጠበቀ የመረጃ ማከማቻ ቋት ( Geospatial Database ) ያደራጃል፡፡
- የክልሉን ሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና ጂኦስፓሻል ዳታ ቤዝ ደህንነትን የማስጠበቅ ስራን ያከናዉናል፡፡
- በክልሉ የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ዘመናዊ የሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና ጂኦስፓሻል መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
- የአሰራር ሥርዓት ትግበራን የሚያቀላጥፉ ደንቦች፣መመሪያዎችና ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፤አፈጻጸማቸዉንም ይከታተላል፡፡
- በሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና ጂኦስፓሻል መረጃዎች ዙሪያ የሚካሄዱጥናቶችን ያስተባብራል፣ የጥናትና ምርምር ዉጤቶችን መሰረት በማድረግ የዉሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
- የጥናትና ምርምር ዉጤቶችን ሳይንሳዊ ደረጃቸዉን ጠብቀዉ እንዲታተሙ ያደርጋል፡፡
- የባለሙያዎችን ዕዉቀትና ክህሎት ለማሳደግ የአጭር ፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ስልጠና የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል ፤ ያበቃል፡፡
- የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ለማሳደግ ተከታታይነት ያላቸዉን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡ ዉጤታማነታቸዉንም ይገመግማል፡፡
- የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን በማጠናከር ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣሙ የሶሽዮ-ኢኮኖሚ እና ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማትና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲመረጡ ያደርጋል፣ ልምድ እንዲቀሰምና ተቀምሮና ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
- የክልሉን አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳይ መረጃን የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት አስተዳደር ስርዓትን በመጠቀም፣ በበይነ-መረብ(website)፣ በሕትመት እና በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ ዘዴዎች ለተገልጋዮችና የዉሳኔ ሰጪዎች ተደራሽ ያደርጋል፡፡