- የተለያዩ የሥነ-ህዝብ ደንብ፣ መመሪያ፣ የሥልጠና እና ስትራቴጂ ሰነድ ማዘጋጀትና ማሻሻል፤
- በሥነ-ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጐልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ሥራዎችን ለማስፈጸም የሚረዱ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አፈጻጸማቸውን መገምገም፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
- በሁሉም አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች የሥነ-ሕዝብ ክበባትን በማቋቋም፣ ውጤታማነታቸውን በመከታተል፣ በተለያዩ ቁሳቁሶች በመደገፍ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድርን ማስተባበር፤
- የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ለአመራሩ (ለውሳኔ ሰጪ አካላት) እና ለህብረተሰቡ በሥነ-ሕዝብ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ለሥነ-ህዝብ ችግሮች የመፍትሄ ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል፤
- የማህበረሰብ ውይይቶችን በማካሄድ የሥነ-ሕዝብ ችግሮችን የመከላከልና የመፍታት ሥራዎችን ማቀድ፣ ማስተባበርና መምራት፤
- የሥነ-ህዝብ ቀን በዓል አከባበር ሥራን ማቀድ፣ መምራት፣ ማስተባበር፤
- የሥነ-ሕዝብ መልዕክቶችን የያዙ የተለያዩ መጽሄቶች፣ብሮሸሮች፣ቡክሌቶች እና የመሳሰሉትን አዘጋጅቶ በማሳተም ለህብረተሰቡ ማሰራጨት፤
- በሥነ-ሕዝብ ችግሮች ዙሪያ ተከታታይ ት/ት ሰጪ መልዕክቶችን /ስክሪፕት/ በማዘጋጀት በሬዲዮ እንዲተላለፍ ማድረግ፤