የማክሮ ኢኮኖሚና ፖሊሲ ማኔጅመንት ጥናትና ትንተና ዳይሬክቶሬት
- ክልላዊ ሀብት ግመታና የኢኮኖሚ ዕድገት ጥናት ያካሂዳል፤
- ክልላዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል፤
- የክልላዊ ሀብት ማከፋፈያ አመልካቾችን በየጊዜው ጥናት በማድረግ ይበልጥ ፍትሐዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
- በክልሉ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር አሠራር ላይ ለክልልና አስተዳደር እርከኖች እንዲሁም አግባብ ላላቸው ባለድርሻ አካላት ስልጠና ይሰጣል፤
- የክልሉን የድህነት ገጽታ ጥናት ያካሂዳል፤
- ከፌደራል የህግ ማዕቀፍ ጋር እንዲጣጣም በማድረግ ክልላዊ ፖሊሲ ያዘጋጃል፤
- የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አፈፃፀም ጥናት ያካሂዳል፤
- በተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናት ያካሂዳል፤ የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፤
- በሥራ ላይ የዋሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ያስገኙትን ፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፤
- የቁጠባና ኢንቨስትመንት ምጣኔ ጥናት ያደርጋል፤
- በተገኙ የጥናት ውጤቶች ላይ በመመሥረት ለአስፈፃሚ አካላት ለፖሊሲ ግብአት ያቀ