- የክልሉን የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ይገመግማል፤ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤
- የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቅፍ ያዘጋጃል፤ ለመስተዳድር ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፤
- የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል፤ ይገመግማል፤ያስፀድቃል፤
- በክልሉ የታችኛውን የአስተዳደር ዕርከን ዓመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጅል፣ለክልሉ ምክር ቤት እንዲጸድቅ ያቀርባል፣
- የክልሉን የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፣
- የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አፈፃፀም ጥናት ያካሂዳል፤
- የክልሉን የልማት ክፍተት እና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል፤
- የክልሉን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ጥናት ያደርጋል፣
- የክልሉን የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ያስፀድቃል፤
- የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ ያዘጋጃል፤ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በማቅረብ ያስፀድቃል፤
- ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡