• (+251)462125955
  • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

የመንግስት ኮሙኒክሽን ዳይሬክቶሬት

  1. የተቋሙ የበላይ ኃላፊ የቃል አቀባይ ኃላፊ ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የቃል አቀባይነት ሥራን ይሰራል፣
  2. የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዓመታዊ የኮሙኒኬሽን ዕቅድ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ጋር አጣጥሞ ማዘጋጀት ለተቋሙ ሥራ አመራር አቅርቦ ማጽደቅ፣ ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማሳወቅና ተግባራዊ ማድረግ፣
  3. በተቋሙ አስፈላጊውን ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ያለው የሕዝብ ግብኙነት ባለሙያ እንዲፈጠር፣ እንዲስፋፋና እንዲዳብር የተለያዩ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ ማቀድ፣ በሚመለከተው አካል ሲፈቀደም ተግባር ላይ ያውላል፣
  4. ከመሥሪያ ቤቱ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ፕሮግራም ዕቅዶችና አፈፃፀሞች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መልዕክቶች በመቅረፅ በተቋሙ የሥራ አመራር አቅርቦት በማፅደቅ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማሰራጨት፣ ግብረመልስ ማሰባሰብ፣
  5. መስሪያ ቤቱን በተመለከቱና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚዲያ ዘገባ ክትትል በማድረግ ትንተና በማዘጋት ለበላይ ኃላፊ በማቅረብ የኮሙኒኬሽን ሥራን ማማከር፣
  6. የመስሪያ ቤቱ መረጃዎች በአግባቡ የሚሰበብቡበትን የሚደራጁበትን ሥርዓት መዘርጋትና ለሚዲያና ለማንኛውም አካል የመረጃ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ወይም አግባብ ካላው የተቋሙ አካላት ምላሸ እንዲሰጥበት ማድረግ፣
  7. በተለያ ጊዜያት ከመንግስት የሚወጡ ወቅታዊ መልዕክቶችን ተቀብሎ ለህዝብ ግንኙነት ስራው ጥቅም ላይ ማዋል፣
  8. በህብረተሰቡ፣ ባለድርሻ አካላትና በተቋሙ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲቻል የተለያዩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ፣
  9. በመስሪያ ቤቱ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች እንዲሁም ለብሔራዊ መግባባት እና ለገጽታ የሚረዱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥና ግልጸኝነትን ለመፍጠር የውይይት መድረኮች ማዘጋጀትና ማስተባበር፣
  10. በመስሪያ ቤቱ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች እንዲሁም ለብሔራዊ መግባባት እና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ግልጸኝነት ለመፍጠር የውይይት መድረኮች ማዘጋጀትና ማስተባበር፣
  11. በመስሪያ ቤቱ የሥራ ሂደቶች መካከል ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት መዘርጋት፣ ማስተባበር፣ ማስፈጸም፣
  12. የመስሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች የመስሪያ ቤቱን የልማት እንቅስቃሴዎች አፈፃፀሞችና ክንውኖች እንዲጎበኙ ማቀድ ማስተባበርና ማስፈጸም፣
  13. ለብሔራዊ መግባባትና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ ነባርና አዳዲስ ዋና ዋና ክልል አቀፍ፣ ሀገር አቀፍና የዓለም አቀፍ ሁነቶች ላይ እንዲሁም የፈጠራ ሁነቶችን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመመካከር ማቀድ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፣
  14. ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንደአስፈላጊነቱ የመስሪያ ቤቱን ፖሊሲዎች፣ ስትራቲጂዎች፣ እቅዶች፣ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶችን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ፕሮግራም ዝግጅቶችን ያቅዳል፣ ያደራጃል ያስፈጽማል፣
  15. በተቋሙ ድረ-ገፅ ላይ የሚጫኑ መረጃዎች ይዘት የመንግስት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የተቋሙን ተልዕኮ ያገናዘበና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ድረ-ገፅ ጋር በተመጋገበ መልኩ እንዲጫን ያደርጋል፣
  16. የመስያ ቤቱን መረጃዎች በፎቶግራፍ በኦዲዮና ቪዲዮ ቀረጻና ህትመት በሥራ ክፍሉ እና በተባባሪዎች አማካኝነት ማዘጋጀትና ጥቅም ላይ ማዋል፣ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በየጊዜው መረጃዎችን አደራጅቶ መስጠትና እንደአስፈላጊነቱ የሥራ ትብብር ማድረግ፣
  17. መስሪያ ቤቱን የሚመለከቱ የማስታወቂያ ሥራዎች በመንግስት በሚመጡ የማስታወቂያዎችና የስፖንሰርሺፕ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ ለሕዝብ ግልጽ እና ትክክለኛ የሆነ መልዕክት ይዘው መውጣታቸውን እና ሥርጭታቸውንም የማስታወቂያ አዋጅ 759/2004ን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ
  18. በመስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ ጥናት ማካሄድ፣ አስተያየት ማሰባሰብ መገምገም፣ አሰራሩ የሚሻሻልበትን አቅጣጫ መቀየስ እና ጥናቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
  19. በክልሉ እና በተቋም ደረጃ ያልተጠበቀ ክስተቶች/ቀውስ/ ሲፈጠር ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ ክስተቶችን ቀውሶችን/ በመገንዘብ ማቀድና ተግባራዊ ማድረግ፣ ሌሎች አካላት ጋር በመመካከር መረጃ ማሰራጨትና የማረጋጋት ተግባር ማከናወን፣ በሶስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የስድስት ወር፣ በዘጠኝ ወር እና በዓመት ወቅቱን ጠብቆ ለበላይ አካልና ለመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማቅረብ፣ በተጨማሪም በተደራጀው የፌዴራል የሕዝብ ግንኙነት ፎረም ላይ ሪፖርቱን አቅርቦ በማስገምገም የሚሰጠውን ግብረ መልስ ተግባራዊ ማድረግ፡፡