የፕላን ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የረጅም ጊዜ መሪ ፕላን ያዘጋጃል፤ ያሳውቃል፤
- የመካከለኛ ጊዜ መሪ ፕላን ያዘጋጃል፤ ያስፀድቃል፤
- የዕቅድ አፈፃፀም ትግበራ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
- የዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ መመሪያ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የረጅምና መካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አፈፃፀም አጋማሽና ማጠቃለያ ግምገማ ያካሂዳል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
- በረጅምና መካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ስልጠና ይሰጣል፤
- የመካከለኛና ረጅም ጊዜ ዕቅዶች አፈፃፀም ፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፤ የጥናት ውጤቱን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤