- በአስተዳደር እርከኖች ያለውን የልማት ክፍተትና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል፤
- የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤
- የካፒታል ፕሮጀክቶች ምዘናና መረጣ የህግ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የካፒታል ፕሮጀክቶች ስርጭት ፍትሐዊነት የአሠራር መመሪያ ያዘጋጃል፤ ይከታተላል፤
- ዓመታዊ የካፒታል ፕሮጀክቶች ፕሮፋይል መረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) ያዘጋጃል፤
- የልማት ፕሮጀክቶች አዋጪነት ጥናት ያካሂዳል፤ ቅደም ተከተል በማስያዝ በበጀት እንዲደገፍ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤
- የሩብ ዓመት፣ የስድስት ወር እና ዓመታዊ የካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤
- በካፒታል ፕሮጀክቶች የግምገማ ግኝቶች ላይ በመመስረት ግብረ መልስ ያዘጋጃል፤ ያስተላልፋል፤
- በተሰጠው ግብረ መልስ መሠረት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ይሰጣል፤ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤