• (+251)462125955
 • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

የልማት መረጃና ስነ-ህዝብ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊነትና ተግባር

 • የክልሉን የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚዉሉ የልማት መረጃዎች በየአስተዳደር እርከኑ እንዲሰበሰቡ ያደርጋል፤አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ይገመግማል::
 • በአስተዳደራዊ መዛግብት (Administrative Records) እና  በጥናት (Survey) ላይ ተመስርቶ ክልላዊ መረጃዎችን ያመነጫል፡፡
 • ክልላዊ ስፓሻል ፕላን ያዘጋጃል፤ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት  የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች  ፍትሃዊ ስርጭት፣ተስማሚ ቦታ መረጣ እና የአዋጪነት ጥናት  ያካሂዳል::
 • ለፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል አጋዥ የሆኑ መሰረታዊ የቀመር መረጃዎችን ያዘጋጃል፡፡
 • የክልሉን መንግስት የልማት እና መልካም አስተዳደር ዉሳኔዎች በተጨባጭ መረጃ  እንዲመሰረት የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ያካሂዳል፡፡
 • የክልሉን የልማት ክፍተት(Development Gap) እና የመልማት አቅም(Development Potential) በመለየት ለፖሊሲ አዉጪዎችና ዉሳኔ ሰጪዎች ያቀርባል፡፡
 • በክልሉ የሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ ልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ተግባራትን በጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ በመደገፍ  ዉጤታማነታቸዉን ለማሳደግ ይሰራል፡፡
 • የክልሉን የማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና የተፈጥሮ ሀብቶችን የሚያሳዩ  ካርታዎችን (thematic map) እና አትላሶች ያዘጋጃል፡፡
 • የክልሉን ስታቲስቲካል እና ጂኦስፓሻል ዳታ ማእከል ያደራጃል፣ ደህንነቱንም የማስጠበቅ ስራን ያከናዉናል፡፡
 • የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች በሥራቸው ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን ስታንዳርዱንና ጥራቱን ጠብቀዉ በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣ በመተንተን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲያደርጉ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
 • የመረጃ ጥራት ቁጥጥር ኦዲት ያደርጋል፡፡ በመረጃዎች ኦዲት   ግኝት መሠረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
 • የክልሉን የስታቲስቲክስና መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራውን ያስተባብራል፤ ይመራል፤
 • የክልሉ የህዝብ እድገት ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የልማት አጋሮችንና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የትምህርትና ቅስቀሳ ተግባራትን ያከናዉናል፡፡
 • የሥነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፡፡
 • የሥነ ህዝብና ልማት ጉዳዮችን በተመለከተ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ያከናውናል፤
 • በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ ህዝብ ምክር ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ5 ዓመት የሥነ ህዝብ ፕሮግራም ያዘጋጃል፤ ለሥነ ህዝብ ም/ቤቱ በማቅረብ ያስፀድቃል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
 • የክልሉን የስታቲስቲክስና መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራውን ያስተባብራል፤ ይመራል፡፡ 
 • በክልሉ የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ  እንዲኖር ዘመናዊ  የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡ የአሰራር ሥርዓት ትግበራን የሚያቀላጥፉ ደንቦች፣መመሪያዎችና ማኑዋሎች  እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፤አፈጻጸማቸዉንም ይከታተላል፡፡
 • የክልሉን ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲሞግራፊያዊ፣ ጂኦስፓሻል እና ስነ-ህዝብ መረጃዎችን በማሰባሰብ በማደራጀትና በመተንተን ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ለተገልጋዮች ለዉሳኔ ሰጪዎች፣ ለፓሊሲ ቀራጮች፣ ለዕቅድ አዉጪዎች ፣ለፕሮጀክትና ፕሮግራም አዘጋጆች እንዲሁም ለትምህርትና ምርምር ሥራዎች እንዲዉሉ የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት አስተዳደር ስርዓትን በመጠቀም፣ በበይነ-መረብ(website)፣ በሕትመት እና በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ ዘዴዎች ተደራሽ ያደርጋል፡፡
 • በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ፈጻሚዎች፣ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን  ይሰጣል፡፡
 • ከባለድርሻ ጋር በመሆን በዕቅድና ፕሮጀክቶች ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
 • የዘርፉን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡