• (+251)462125955
  • SNNPRS, Hwassa Ethiopia

ስታቲስቲክስ ዳይሬክቶሬት

የክልሉን የስታቲስቲካል መረጃዎችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቱን ሊያሳይ በሚችል መልኩ ለተገልጋዩ በማዘጋጀት በክልሉ ለሚካሄደው የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ስራ፤ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር እና የልማት ዕቅዶች ዝግጅት በዋና ግብዓትነት የሚያገለግሉ ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎች በሚፈለገው የክልል አስተዳደር እርከን እንዲቀርቡ በማስቻልና የልማት ክፍተትና የመልማት አቅም በጥናት በመለየት የአቅም ግንባታ በማከናወን ክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን በማጠናከር” ከፌደራል መስሪያ ቤቶች፤ ከሴክተር ቢሮዎች እና ከታችኛው አስተዳደራዊ መዋቅሮች (ዞን፤ልዩወረዳ&ወረዳ፤ከተሞችና ቀበሌዎች) በቢሮዉ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ዲሞግራፊያዊ &የተፈጥሮ ሀብቶችን፤ አስተዳደራዊ መረጃዎችን በመተንተን፤የክልሉን መረጃ ኦዲት በማድረግ ጥራትን በማስጠበቅ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት&ደህንነታቸውን በመጠበቅ በዘመናዊ የመረጃ ዳታ ቤዝ በማደራጀት ለመረጃ ተጠቃሚዎች በሚያመች መንገድ አደራጅቶ፤በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ ዘዴዎች በህመትና በድህረ ገፅ (Hard and soft copy, website) ባሉበት ቦታ ተደራሽ በማድረግ የክልሉን የመረጃ አጠቃቀምና አቅርቦት ማሳደግና ዘመናዊ ማድረግ ነው፡፡