መግቢያ

እንኳን ወደ ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ድረገፅ በሰላም መጣችሁ፡፡
ቢሮዉ የክልሉን የመረጃ ክፍተት ለማሟላት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያከናዉናል፣ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀማቸዉን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አፈፃፀም ጥናት ያካሂዳል፣ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ለመስተዳድር ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፣ የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል፤ ይገመግማል፤ ያስፀድቃል፣ በክልሉ የታችኛዉን የአስተዳደር ዕርከን ዓመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል፣ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፣ የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸዉ አካላት ያቀርባል፣ የልማት ክፍተት እና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል፣ የክልሉን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ጥናት ያደርጋል፣ የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ያስፀድቃል፣ የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በማቅረብ ያስፀድቃል፣ የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና መልክአ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፤ ትንተና በማድረግ አሳቲሞ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልክዓ ምድራዊ ገፅታን የሚያሳይ አትላስና ካርታ ያዘጋጃል፣…Read More
የተቋሙ ሥልጣንና ተግባር
- የክልሉን የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፡፡
- የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ለመስተዳድር ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፤
- የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጪነት ጥናት ያካሂዳል፤ ይገመግማል፤ ያስፀድቃል፤
- የክልሉ የታችኛው የአስተዳደር እርከን ዓመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል፤ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፤
- የክልሉን የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደፈርጋል፤ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፤
- የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አፈፃፀም ጥናት ያካሂዳል፤
- የክልሉን የልማት ክፍተት እና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል፤
- የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ጥናት ያደርጋል፤
- የክልሉን የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ያስፀድቃል፤